የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መገናኛ ዲስትሪክት ጋር የCBE በእጀ አገልግሎት የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ፡፡
የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መገናኛ ዲስትሪክት ጋር የCBE በእጀ አገልግሎት የስምምነት ሰነድ ተፈራረመ፡፡
የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዩጵያ ንግድ ባንክ መገናኛ ዲስትሪክት ጋር ለመምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች ያለማስያዣ የብድር አገልግሎት ማስገኘት የሚችል CBE በእጀ የተባለ የስምምነት ሰነድ ታህሳስ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ተፈራረመ፡፡
የስምምነት ሰነዱን በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በኩል ፕሬዚዳንቱ ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር)፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መገናኛ ዲስትሪክት በኩል የዲስትሪክቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሊያ ተስፋዬ ፈርመዋል፡፡ ስምምነቱ፣ የዩኒቨርሲቲውን መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች CBE በእጀ የድጅታል አነስተኛ ብድር እና ቁጠባ አገልግሎት /DMSL/ ተጠቃሚ ማድረግን ዓላማ ያደረገ መሆኑ በመርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡
የፊርማ መርሐ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ እስካሁን ባለው አሰራር ባንኮች የብድር አገልግሎት የሚሰጡት ማስያዣ ማቅረብ ለሚችል ባለሀብት እና እራሳቸው ለሚያስተዳድሯቸው ሰራተኞቻቸው ብቻ እንደነበረ አስታውሰው፣ “ዛሬ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር የምንፈራረመው ስምምነት፣ ባንኩ ተደራሽነቱን ወደ ዝቅተኛው የማህበረሰብ ክፍል እያሰፋ ለመሆኑ እንደማሳያ የሚወሰድ ነው፤ ከዚህም አልፎ ዜጎች ለባንኩ የባለቤትነት ስሜት እንዲሰማቸው የሚያደርግ ተግባር ነው” ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመገናኛ ዲስትሪክት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሊያ ተስፋዬ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለላፉት 83 ዓመታት ሀገራችንን በፋይናንስ ዘርፍ እያገለገለ እና የተለያዩ ሜጋ ፕሮጀክቶችን እየደገፈ የተሻገረ ግዙፍ የፋይናንስ ተቋም መሆኑን አውስተው፣ “ባንካችን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሀብት እንደመሆኑ መጠን፣ የደንበኞቻችንን የረጅም ጊዜ ጥያቄ መሰረት በማድረግ ለሁሉም ደንበኞቻችን የብድር አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ የተመቻቸውን CBE በእጀ የብድር እና የቁጠባ አገልግሎት ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ስናቀርብ ታላቅ ደስታ ይሰማናል” ብለዋል፡፡
ከዚህ በመቀጠልም የዩኒቨርሲቲው መምህራን እና ሰራተኞች ባንኩ የሚሰጣቸውን የአጭርና የረጅም ጊዜ የብድር አገልግሎቶች አስመልክተው ላቀረቧቸው ጥያቄዎች የባንኩ ሙያተኞች ማብራሪያ እና ገለጻ ሰጥተው የፊርማ መርሐ ግብሩ ተጠናቋል፡፡
Follow our Facebook page: https://web.facebook.com/EPSUfb
Follow our Telegram Channel: https://t.me/epsutelegram
PR call: 0945746405